የሀገር ውስጥ ዜና

በሆሮ ጉድሩ  ህገወጥ የጦር መሳሪያ ተያዘ

By Tibebu Kebede

March 31, 2021

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 22፣ 2013 (ኤፍቢሲ) በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን በሕገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ የጦር መሣሪያ በቁጥጥር ሥር መዋሉን ፖሊስ አስታወቀ።

የዞኑ ፖሊስ መምሪያ የመረጃ ክፍል ባለሙያ ሳጂን ኦላና ተክሉ ፤ የጦር መሳሪያው የተያዘው በዞኑ በአሙሩ ወረዳ በአገምሣ ፍተሻ ኬላ ላይ መሆኑን ተናግረዋል።

በወረዳውና በክልሉ ልዩ ሀይል ፖሊሶች በተደረገ ፍተሻ የጦር መሳሪያው መያዙን ነው የገሉፀት ።

በፍተሻው ከተያዙት የጦር መሳሪያዎች ሶስት ክላሽንኮቭ ጠመንጃዎች፣ 16 ቱርከ ሰራሽ ሽጉጦች፣ 5 ሺህ 855 የክላሽ፣ የብሬልና የሽጉጥ ተተኳሽ ጥይቶች መሆናቸውን መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

በጦር መሳሪያዎቹ ዝውውር የተጠረጠሩ አራት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተካሄደባቸው መሆኑን አስታውቀዋል ።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!