ቢዝነስ

አማራ ብድርና ቁጠባ ተቋም ወደ ባንክነት ተሸጋገረ

By Tibebu Kebede

April 03, 2021

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 25 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አማራ ብድርና ቁጠባ ተቋም (አብቁተ) “ፀደይ ባንክ” በሚል መጠሪያ ወደ ባንክነት ሽግግር አድርጓል።

የተቋሙን ወደ ባንክነት ሽግግር አስመልክቶ የባለአክሲዮኖቹ ጉባዔ ዛሬ በባሕር ዳር ተካሂዷል።

በዝግጅቱ ላይ የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አገኘሁ ተሻገር እና የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ አቶ ገዱ አንዳርጋቸውን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እና ባለአክሲዮኖች መገኘታቸውን ኢቢሲ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!