ዓለምአቀፋዊ ዜና

አፍሪካ ለኮሮና ቫይረስ ክትባት የሚውል 12 ቢሊየን ዶላር እንደሚያስፈልጋት ተገለጸ

By Meseret Awoke

April 06, 2021

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 28፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) አፍሪካ ለኮሮና ቫይረስ ክትባት የሚውል 12 ቢሊየን ዶላር እንደሚያስፈልጋት የዓለም ባንክ ገልጿል፡፡

እንደዓለም ባንክ ሪፖርት ከሆነ ገንዘቡ በቂ የኮሮና ቫይረስ ክትባት ለመግዛትና ለማሰራጨት የሚውል ነው፡፡

በሌላ በኩል የቡድን 20 አባል አገራት ለአለም ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ሃገራት በሚሰጡት የእዳ ክፍያ ላይ የእፎይታ ጊዜያቸውን ማራዘም እንዳለባቸውም ተገልጿል፡፡

የዓለም ባንክ እና አይኤምኤፍ በክትባት ፣ በእዳ ፣ በኢኮኖሚ ማገገም ፣ በአየር ንብረት ለውጥ እና በሌሎች ዙሪያ ለመምከር በዚህ ሳምንት እንደሚሰበሰቡ ታውቋል፡፡

ምንጭ፡- ቢቢሲ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!