ስፓርት

ኢትዮጵያ ቡና ኤርትራዊውን ሮቤል ተክለሚካኤልና ናትናኤል በርሔን አስፈረመ

By Tibebu Kebede

April 07, 2021

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 29፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብን ሁለት ተጫዋቾችን ማስፈረሙን አስታውቋል።

ኢትዮጵያ ቡና የኤርትራ ብሔራዊ ቡድን አንበል እና የቀይ ባህር እግር ኳስ ክለብ ተጫዋች የነበረው እና የሴካፋ ሀገራት ውድድር ላይ የውድድሩ  ኮከብ ተጫዋች ተብሎ የተመረጠውን ሮቤል ተክለሚካኤል ማስፈሙን ነው የገለፀው።

በተጨማሪም ለደደቢት እንዲሁም ለከፋ ቡና የተጫወተውን ናትናኤል በርሔን እንዳስፈረመ በክለቡ ይፋዊ የፌስቡክ ገፅ ላይ ገልጿል።

ሁለቱ ተጫዋቾች እስከ ሰኔ 30 ቀን 2014 ዓ.ም የሚያቆያቸውን ስምምነት ከክለቡ ጋር ተፈራርመዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-

https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!