የሀገር ውስጥ ዜና

አቶ ደመቀ መኮንን ከባይደን የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ ጃክ ሱሊቫን ጋር ተወያዩ

By Abrham Fekede

April 08, 2021

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 30፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን የብሔራዊ የደህንነት አማካሪ ጃክ ሱሊቫን ጋር በስልክ ተወያዩ፡፡

አቶ ደመቀ በትግራይ እየተሻሻለ ስላለው ሁኔታ ለብሔራዊ የደህንነት አማካሪ ማብራራታቸውን አስታውቀዋል፡፡

እንዲሁም በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት ሰሞኑን በተካሄደው በታላቁ የሕዳሴ ግድብ ዙሪያም ተወያይተዋል፡፡

በተጨማሪም ከኢትዮ-ሱዳን ድንበር ጋር በተያያዘ ጉዳዩ በሰላማዊ መንገድ መፍትሔ እንደሚያገኝ እንዳረጋገጡላቸው ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!