የሀገር ውስጥ ዜና

ፕሬዚደንት ሣህለ ወርቅ ከካናል ፕላስ ግሩፕ የአፍሪካ ማናጀር ጋር ተወያዩ

By Meseret Awoke

April 12, 2021

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 4፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)ፕሬዚደንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ በቴሌቪዥን ኢንደስትሪው ግንባር ቀደም ከሚባሉት መካከል የሚመደበው የካናል ፕላስ ግሩፕ የአፍሪካ ማናጀር ጋር ተወያይተዋል::

በመዝናኛው የቴሌቪዥን መስክ ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ በማፍሰስ እና ጥሩ የሚባሉ አዝናኝ እና አስተማሪ ፕሮግራሞችን በማቅረብ ዝነኛ የሆነው ካናል ፕላስ በኢትዮጵያም ፅህፈት ቤት በመክፈት ስራ መጀመሩን ስራ አስኪያጁ አብራርተዋል::

ፕሬዚደንት ሣህለ ወርቅ ካናል ፕላስ ኢትዮጵያዊ ለዛና ጣዕም ያላቸው ዝግጅቶችን በመርሀ ግብሩ ማካተቱን አድንቀዋል::

መርሃግብሮቹን ለመዝናኛነት ብቻ ሳይሆን ለማስተማሪያነትም መጠቀም አስፈላጊ መሆኑን አፅንኦት መስጠታቸውንም ከፕሬዚደንት ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል::

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን