የሀገር ውስጥ ዜና

የከተራ እና የጥምቀት በዓላት ያለምንም የጸጥታ ችግር እንዲከበሩ ዝግጅት ማድረጉን ፖሊስ አስታወቀ

By Tibebu Kebede

January 16, 2020

አዲስ አበባ፣ ጥር 7፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የከተራ እና የጥምቀት በዓላት ያለምንም የጸጥታ ችግር እንዲከበሩ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ማድረጉን አስታወቀ።

የኮሚሽኑ የወንጀልና ትራፊክ አደጋ መከላከል ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ፥ የጥምቀት በዓልን አከባበር እና የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን አስመልክተው ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።