የሀገር ውስጥ ዜና

የሥራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን እና ባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ የሥራ ገበያ አካታችነት ጥናት መነሻ ሰነድ ላይ ተወያዩ

By Meseret Awoke

April 13, 2021

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 5፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)የሥራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን እና ባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ በጋራ የሚሰሩት የሥራ ገበያ አካታችነት ጥናት መነሻ ሰነድ ላይ ተወያይተዋል።

ውይይቱ የሥራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽነር አቶ ንጉሡ ጥላሁንና የባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ፍሬው ተገኘ በተገኙበት የተደረገ ነው።

የባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ በተከታታይ ዓመታት በጥናትና ምርምር የተለያዩ ሽልማቶችን ያገኘ ሲሆን፤ ጥናቱን በፋይናንስና በባለሙያዎች ድጋፍ በማድረግ እንደሚሰራ ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የሥራ ገበያው ሴቶችን፣ አካል ጉዳተኞችን፣ መኖሪያቸው በጎዳና የሆኑ ዜጎችን፣ የአገር ውስጥ ተፈናቃዮችንና ከስደት ተመላሾችን ከሕዝብ ቁጥር ምጣኔ አንጻር በተገቢው ሁኔታ ያላካተተ በመሆኑና ጥናቱ እነዚህን የማሕበረሰብ ክፍሎች በሥራ ገበያው ውስጥ ሊካተቱ የሚችሉባቸውን መንገዶች የሚያመላክት መሆኑን መረጃዎች ይጠቁማሉ።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን