የሀገር ውስጥ ዜና

አምባሳደር መለስ ዓለም ከአልጄሪያ አምባሳደር ጋር ተወያዩ

By Tibebu Kebede

January 16, 2020

አዲስ አበባ፣ ጥር 7፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) አምባሳደር መለስ ዓለም በናይሮቢ ተቀማጭነታቸውን ካደረጉት የአልጄሪያ አምባሳደር ሰልማ መሊካ ሃዳዲ ጋር ተወያይተዋል።

በውይይታቸውም በናይሮቢ በሚገኙ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጽህፈት ቤቶች በሚካሄዱ ባለ ብዙ ወገን መድረኮች ላይ በቅርበት መስራት በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ መክረዋል።

አምባሳደሯ በኬንያ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ኤምባሲውን መጎብኘታቸውን በኬንያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

አምባሳደሯ ከዚህ ቀደም በአዲስ አበባ የምክትል የሚሲዮን መሪ በመሆን አገልገለዋል።