የሀገር ውስጥ ዜና

በኢትዮጵያ ቴአትር የተጀመረበት 100ኛ ዓመት የሚዘክር መድረክ ተካሄደ

By Meseret Awoke

April 14, 2021

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 6፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)በኢትዮጵያ ቴአትር የተጀመረበት 100ኛ ዓመት የሚዘክር መድረክ ተካሂዷል፡፡

መድረኩ የኢትዮጵያ ቴአትር ባለሙያዎች ማህበር፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ቴአትር ዲፓርትመንት መምህራንና ተማሪዎች ፣ የቴአትር አድናቂዎችና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ትብብር ተዘጋጅቷል፡፡

መርሃ ግብሩ ‘‘ቴአትር በኔ ዘመን አይሞትም’’ በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀ ሲሆን፤ ለተከታታይ አንድ ወር 100 ቴአትሮች ይቀርባሉ ተብሎም ይጠበቃል፡፡ አላማውም በኮቪድ-19 ምክንያት የተዳከመውን የቴአትር ዘርፍ ለማነቃቃት ያለመ ነው ተብሏል፡፡

በመርሃ ግብሩ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሳው፣ የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤን ጨምሮ አንጋፋና ወጣት የዘርፉ ባለሙያዎች፣ የቴአትር አድናቂዎችና ጥሪ የተደረገላቸው አካላት በመክፈቻ ስነስርዓቱ ላይ ተገኝተዋል፡፡

በስነስርዓቱ ላይ ‘‘ሼክስፔር ኢትዮጵያዊ ነው’’ እና ‘‘የካሳ ፈረሶች’’ የሚሉ ቴአትሮች ለታዳሚያን የቀረቡ ሲሆን፤ የፎቶ አውደርዕይ በመርሃግበሩ ለዕይታ ቀርቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን