የሀገር ውስጥ ዜና

ከባህር ዳር ወደ አዲስ አበባ ሲጓጓዝ የነበረ 108 ሽጉጥና ከ2 ሺህ 800 በላይ ጥይት ተያዘ

By Meseret Awoke

April 14, 2021

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 6፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)መነሻውን ባህር ዳር በማድረግ ወደ አዲስ አበባ ሲጓጓዝ የነበረ 108 ቱርክ ሰራሽ ሽጉጦች እና ከ2 ሺህ 800 በላይ ተተኳሸ ጥይት በማንኩሳ ከተማ ተይዟል፡፡

ህገወጥ የጦር መሳሪያዎችን በመያዝ ወደ አዲስ አበባ ለመውሰድ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ሁለት ተጠርጣሪ ግለሰቦች በምዕራብ ጎጃም ዞን ጃቢጠህናን ወረዳ ማንኩሳ ከተማ ሲደርሱ ከነጦር መሳሪያቸው በቁጥጥር ስር እንደዋሉ የዞኑ ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል፡፡

የምዕራብ ጎጃም ዞን ፖሊስ መምሪያ የሚዲያና ኮምዩኒኬሽን ባለሙያ ዋና ሳጅን መንገሻ ይማም በተካሄደ ፍተሻ የጦር መሳሪያዎቹን መያዝ መቻሉን ገልጸዋል፡፡

በቁጥጥር ስር በዋሉት ሁለት ተጠርጣሪዎች ላይ ምርመራ እየተደረገ መሆኑንም ዋና ሳጅን መንገሻ መግለጻቸውን አሚኮ ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን