የሀገር ውስጥ ዜና

አቶ ደመቀ መኮንን ከዓለም የጤና ድርጅት የአፍሪካ ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ

By Meseret Awoke

April 14, 2021

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 6፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከዓለም የጤና ድርጅት የአፍሪካ ዳይሬክተር ዶክተር ሞኤቲ ሺዲ ጋር ተወያይተዋል፡፡

ውይይቱ ኢትዮጵያ ኮቪድ -19ን ለመከላከል እያደረገች ያለው ጥረትና በአፍሪካ የኮቪድ-19 ክትባት ተደራሽነት ላይ መሆኑን ኢቢሲ ዘግቧል፡፡

በተጨማሪም የዓለም ጤና ድርጅት ለኢትዮጵያ በጤና ዘርፍ የሚያደርገውን ድጋፍ እንደሚቀጥል ዶክተር ሞኤቲ ገልጸዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን