ስፓርት

የፕሪሚየር ሊጉ አሸናፊ 1 ሚሊየን ብር ሽልማት ይበረከትለታል

By Tibebu Kebede

April 15, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 7 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2013 ቤት ኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አሸናፊ የሚሆነው ክለብ የ1 ሚሊየን ብር ተሸላሚ እንደሚሆን የፕሪሚየር ሊጉ አክሲዮን ኩባንያ አስታወቀ፡፡

ኩባንያው ዛሬ በሰጠው መግለጫ ሁሉም ተሳታፊ ክለቦች እንደየ ደረጃቸው ሽልማት የሚበረከትላቸው ሲሆን፥ ሁለተኛ ሆኖ ለሚያጠናቅቅ ክለብ የ700 ሺህ እንዲሁም 3ኛ ሆኖ ለሚጨርስ የ500 ሺህ ብር ሽልማት እንደሚሰጥ ገልጿል።

የፕሪሚየር ሊጉ መርሃ ግብር ሳይጠናቀቅ አሸናፊው ከታወቀ ዋንጫው ለአሸናፊው ቀድሞ እንደሚሰጥ የኩባንያው ውድድር ሰብሳቢ መቶ አለቃ ፈቃደ ማሞ ተናግረዋል።

ፕሪሚየር ሊጉ ግንቦት 18 የሚጠናቀቅ ሲሆን፥ ግንቦት 21 ጠቅላላ ጉባኤ ተጠርቶ የኮኮቦች ሽልማት ይሰጣልም ብለዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!