ዓለምአቀፋዊ ዜና

በዓለም በኮቪድ19 ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 3 ሚሊየንን ተሻገረ

By Meseret Awoke

April 16, 2021

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 8፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በዓለም ዙሪያ በኮቪድ-19 ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 3 ሚሊየንን ተሻግሯል፡፡

በዓለም አቀፍ ደረጃ 139 ሚሊየን 710 ሺህ 700 በላይ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሲያዙ፤ ከ3 ሚሊየን በላይ ሰዎች ደግሞ ለህልፈት ተዳርገዋል፡፡

በአንጻሩ 118 ሚሊየን 763 ሺህ 400 በላይ ሰዎች ከቫይረሱ አገግመዋል፡፡

አሜሪካ፣ ህንድ፣ ብራዚል፣ ፈረንሳይ እና ሩሲያ ቫይረሱ ከጸናባቸው ሃገራት መካከል ቀዳሚውን ደረጃ ይይዛሉ፡፡

ምንጭ፡- ዎርልድ ኦ ሜትር ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን