የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮጵያ እና ሩሲያ በኒውክሌር ሃይል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ

By Tibebu Kebede

April 16, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 8 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጅ ሚኒስቴር እና የሩሲያው የአቶሚክ ሃይል ኮርፖሬሽን በኒውክሌር ሃይል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

ስምምነቱ በኒውክሌር ሃይል የማህበረሰቡን በጎ ግንዛቤ ለማሳደግዳ እና ስልጠና ለመስጠት እንዲሁም ክህሎት ለማሳደግ የሚያስችል ድጋፍ ለመስጠት ያለመ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

ስምምነቱን በሩሲያ የኢትዮጵያ አምባሳደር አለማየሁ ተገኑ እና የሩሲያ የአቶሚክ ሃይል ምክትል ዳይሬክተር ኒኮላይ ስፓስኪ ተፈራርመውታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!