የሀገር ውስጥ ዜና

አሜሪካ በኢትዮጵያ ለጤናው ዘርፍ የ20 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ይፋ አደረገች

By Tibebu Kebede

April 16, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 8 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካ በሽታ መከላከልና መቆጣጠሪያ ማዕከል በኢትዮጵያ ለጤናው ዘርፍ የ20 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ይፋ አደረገ፡፡

ድጋፉ ለኮቪድ19 በሚደረገው ድጋፍና የሃገሪቱን ኢኮኖሚ ደህንነት ለማረጋገጥ በሚተገበሩ ፕሮጀክቶች ማዕቀፍ አማካኝነት መለቀቁን በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ አስታውቋል፡፡

ዛሬ ይፋ የተደረገው ድጋፍም የሃገሪቱን የህብረተሰብ ጤና አቅምን ለማጠናከር የሚውል መሆኑ ተገልጿል፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞም በጤናው ዘርፍ በሽታዎችን ለመለየትና ቀድሞ ለመከላከል፣ የላቦራቶሪ ምርመራ አቅምን ለማጠናከር፣ የክትባት ተደራሽነትን ለማስፋትና ለማጠናከር እንዲሁም በአደጋ ጊዜ ምላሽ የመስጠት አቅምን ለማጠናከር ይውላልም ተብሏል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!