የሀገር ውስጥ ዜና

የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን የስም ለውጥ አደረገ

By Tibebu Kebede

April 16, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 8 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ስያሜ ወደ “ኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን” ተለወጠ፡፡

አዲሱ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን አዋጅ በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ በስራ ላይ ውሏል፡፡

ይህን ተከትሎም ከዚህ በፊት በስራ ላይ የነበረው የብሮድካስት አገልግሎት አዋጅ ቁጥር 533|1999 ተሽሮ ወደ 1238\2013 መለወጡን ከባለስልጣኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ስያሜም ወደ “ኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን” ተለውጧል፡፡

በቅርቡ በህዘብ ተወካዮች ምክር ቤት የፀደቀው ይህ አዋጅ የሃገሪቱን የሚዲያ እድገት በጅጉ ያጎለብታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!