የሀገር ውስጥ ዜና

የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ዳይሬክተር ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ጋር ተወያዩ

By Meseret Awoke

April 16, 2021

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 8፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ዳይሬክተር ዶክተር ማትሺድሶ ሞኤቲ ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ጋር ተወያይተዋል፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት የኮቪድ-19 ድጋፍን ጨምሮ ለክልሉ የሚያደርገውን የሰብዓዊ ድጋፍ ከአጋሮቹ ጋር እየሰራ እንደሚገኝ ዳይሬክተሯ ገልጸዋል፡፡

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢትዮጵያ ተወካይ፣ የሰብአዊ ጉዳዮች አስተባባሪ ካትሪን ሶዚ እና የዓለም ጤና ድርጅት ልዑካን በመቐለ የተፈናቃዮች መጠለያ ጣቢያን ጎብኝተዋል፡፡

በተጨማሪም በክልሉ የሰብአዊ ድጋፍ እያደረጉ ከሚገኙት የተባበሩት መንግስታት አጋር አካላት ጋር በመገናኘት መወያየታቸውን ከአለም ጤና ድርጅት በኢትዮጵያ የትዊተር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!