ስፓርት

በፕሪሚየር ሊጉ ሰበታ ከተማ ጅማ አባ ጅፋርን አሸነፈ

By Tibebu Kebede

April 16, 2021

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 8፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በፕሪሚየር ሊጉ ሰበታ ከተማ ጅማ አባ ጅፋርን 2 ለ 1 አሸነፈ።

በጨዋታው ጅማ አባ ጅፋር ሱራፌል አወል በ32ኛው ደቂቃ ላይ ባስቆጠረው ግብ ቀዳሚ መሆን ችለው የነበረ ቢሆንም ከእረፍት መልስ ኦሲይ ማውሊ ባስቆጠራቸው ግቦች ሰበታ ከተማ ማሸነፍ ችሏል።

የሰበታ ከተማ ማሸነፊያ ግቦችን ኦሰይ ማወሊ በ59ኛው እና 82ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥሯል።