የሀገር ውስጥ ዜና

የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የከተማ መኖሪያ ቤት እጥረትን ለማቃለል የሚያደርጋቸውን ጥረቶች የሚያስደስቱ ናቸው-ጠ/ሚ ዐቢይ

By Tibebu Kebede

April 16, 2021

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 8፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የከተማ መኖሪያ ቤት እጥረትን ለማቃለል የሚያደርጋቸውን ጥረቶች በማየታቸው ደስተኛ መሆናቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለፁ።

በስድስት ወራት ውስጥ በ3 ሄክታር መሬት ላይ በ16 ሕንፃዎች 500 ቤቶችን በ3 ቢሊየን ብር ኮርፖሬሽኑ መገንባቱን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የከተማ የመኖሪያ ፍላጎትን ለማሟላት፤መንግሥት እንደዚህ ያሉ ተቋማቶን ማጠናከሩን ይቀጥላል ብለዋል።