የሀገር ውስጥ ዜና

የባህልና ቱሪዝም ዘርፍ ለህዝቦች የእርስ በእርስ ግንኙነት መጠናከር ሚናው ከፍ እንዲል መደረግ አለበት – ዶ/ር ሂሩት ካሳው  

By Tibebu Kebede

April 17, 2021

 

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 9 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)- የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የ2013 በጀት ዓመት የ9 ወራት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት በሐረር ከተማ እየቀረበ ይገኛል፡፡

የባህልና ቱሪዝም ሚንስትር ዶ/ር ሂሩት ካሳው ለዘርፉ እድገት የልምድ ልውውጥ በማድረግ ሴክተሩ የህዝቦች እርስ በእርስ ግንኙነትን በማጠናከር በሀገራችን ፍቅር፣ ሰላም እና አንድነት እንዲፈጠር በጋራ  ለመስራት የምናቅድበት ጊዜ ነው ብለዋል፡፡

የሀረሪ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ አቶ ዲኒ ረመዳን ፣ክልሎች ዕርስ በዕርስ የልምድ ልውውጥ የምናደርግበት እንዲሁም ዘርፉ ለህዝባችን አንድነትና ሰላም ያለውን ድርሻ ለማሳደግ በትብብር መስራት ይገባናል ብለዋል፡፡

የ9 ወራት እቅደ አፈፃፀም ሪፖርት እና የቀጣይ ቀሪ ወራት እቅድ የሚቀርብበት መድረክ መሆኑን ከባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!