የሀገር ውስጥ ዜና

የ10 ዓመቱ ሃገራዊ የልማት ዕቅድ ሰነድ ተለቀቀ

By Abrham Fekede

April 19, 2021

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 11፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የፕላን እና ልማት ኮሚሽን ያዘጋጀው የ10 ዓመቱ የልማት ዕቅድ ሰነድ በዛሬው ዕለት በቀጥታ (ኦንላይን) ላይ ተለቀቀ፡፡

ይህንኑ የልማት እቅዱን ‹ሶፍት ኮፒ› በዋነኝነት የፕላን እና ልማት ኮሚሽን ድረ ገጽ (http://www.pdc.gov.et/#/tenyearplansection) ሊንክ ተጭነው ማግኘት እንደሚቻል ኮሚሽኑ አስታውቋል።

በሌላ በኩል በመጽሐፍ መልክ የተሰናዳው ሰነድ በህትመት ሒደት ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ የህትመት ሒደቱ ሲጠናቀቅ በተመሳሳይ ለሕዝብ ይደርሳል ተብሏል።

በኢትዮጵያ በቀደሙት ዓመታት የልማት ዕቅድ ትግበራ ክፍተቶችን እንዲሁም የተመዘገቡ ጠንካራ ጎኖችን ከግምት በማስገባት በቀጣዮቹ 10 ዓመታት የኢትዮጵያን የብልጽግና ጉዞ ለማሳለጥ እንዲረዳ የተዘጋጀ ዕቅድ መሆኑን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የተቀመጠውን ኢትዮጵያን “አፍሪካዊት የብልጽግና ተምሳሌት” የማድረግ ሀገራዊ የልማት ራዕይ ለማሳካት ጉልህ ሚና ይኖረዋል ተብሎ የተዘጋጀው ይህ የልማት ዕቅድ ባሳለፍነው መጋቢት ወር ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ መጽደቁ ይታወሳል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!