የሀገር ውስጥ ዜና

ከሻሸመኔ ወደ ሞያሌ ሲጓጓዝ የነበረ ከዘጠኝ ኩንታል በላይ አደንዛዥ ዕጽ ተያዘ

By Meseret Awoke

April 19, 2021

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 11፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ከሻሸመኔ ወደ ሞያሌ ሲጓጓዝ የነበረ ካናቢስ የተባለ ዘጠኝ ኩንታል ተኩል አደንዛዥ ዕጽ መያዙን ፖሊስ አስታወቀ።

በኦሮሚያ ክልል የቦረና ዞን ፖሊስ መምሪያ የወንጀል መከላከል አስተባባሪ ተወካይ ዋና ሳጂን ሲሳይ መገርሳ እንደገለጹት፥ አደንዛዥ ዕፁ መነሻው ሻሸመኔ ሆኖ ወደ ሞያሌ ለማጓጓዝ ታስቦ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3- 70251 አዲስ አበባ በሆነ አይሱዙ ተሽከርካሪ ላይ ተጭኖ ዌብ ቀበሌ እንደደረስ በፖሊስ ክትትል መያዙን ተናግረዋል።

አሽከርካሪው ለጊዜው ከአካባቢው ሸሽቶ ቢያመልጥም ፖሊስ ክትትል እያደረገበት መሆኑን አስረድተዋል፡፡

በአቋራጭ ለመበልጸግ በህገወጥ ተግባር የተሰማሩ ግለሰቦችን በማጋለጥ የዞኑ ህዝብ የጀመረውን ትብብር አጠናክሮ እንዲቀጥል መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ህገ ወጦችን ለመከላከል ከፍትህ አካላት የተውጣጣና በዞኑ አስተዳዳር የሚመራ የጸረ ኮንትሮባንድ ግብረ ሃይል መቋቋሙንም መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በቦረና ዞን ህዝብ ጥቆማ ባለፉት ዘጠኝ ወራት 17 ሺህ 600 ኪሎ ግራም የሚመዝን አደንዛዥ ዕጽ መያዙንም አስታውሰዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!