Fana: At a Speed of Life!

ሃገር አቀፍ የክህሎት የቴክኖሎጂ እና የተግባራዊ ጥናትና ምርምር ውድድር ሲምፖዚየም ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 12፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ሁለተኛው ሃገር አቀፍ የክህሎት፣ የቴክኖሎጂ እና የተግባራዊ ጥናትና ምርምር ውድድር ሲምፖዚየም እና አውደ ርዕይ ተጀምሯል፡፡

መርሃግብሩ ‘‘ክህሎት ያለው ዜጋ ለኢትዮጵያ ብልጽግና ’’ በሚል መሪ ሃሳብ የሚካሄድ ነው ፡፡

አሁን ላይ በኢትዮጵያ ከ1ሺህ 600 በላይ የመንግስትና የግል የቴክኒክና ሙያ ተቋማት የሚገኙ ሲሆን፤ ውድድሩ ከእነዚህ ተቋማት የተውጣጡ አሰልጣኝና ሰልጣኞች እንዲሁም ከመላው ኢትዮጵያ የተውጣጡ ከጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች በየደረጃው ተወዳድረው በክልል ደረጃ አሸናፊ የሆኑት የሚወዳደሩበት ነው።

በዚህም ክህሎት ያላቸውን ዜጎች አቅማቸውን ለህብረተሰቡ የሚያሳዩበት፣ ልምድና ተሞክሯቸውን የሚለዋወጡብት እንደሆነም ተነስቷል፡፡

መርሃግብሩ ከክህሎት፣ከቴክኖሎጂ ውድድር ባለፈ የተግባራዊ ጥናትና ምርምርን ጨምሮ ሲምፖዚየምንና አውደ ርዕይን ያካተተ ነው፡፡

ሙያንና የሙያ ትምህርትና ስልጠናን በማስተዋወቅ ወጣቶች ሙያን እንዲማሩ ብሎም በህብረተሰቡ ዘንድ ለቴክኒክና ሙያ ስልጠና ያለውን የተዛባ አመለካከት መቀየር ዋና አላማው ሲሆን፤ የስራ መፍጠሪያ መንገዶችን ለወጣቶች የሚያመላክቱበት እና አዳዲስ የፈጠራ ሃሳቦች ጎልተው የሚወጡበት እንደሚሆን ታምኖበታል፡፡

በዚህ ውድድር 391 ሰልጣኝ፣ አሰልጣኝና ከጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል ፡፡

በሃይማኖት ኢያሱ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.