የሀገር ውስጥ ዜና

በአማራ ላይ ያነጣጠሩ ጥቃቶች እንዲቆሙ የሚጠይቁ ሠልፍች በአማራ ክልል የተለያዩ ከተሞች ተካሄዱ

By Tibebu Kebede

April 20, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 12 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል ደሴ ፣ ባህርዳር እና ደብረ ማርቆስ እና ወልዲያን ጨምሮ በተለያዩ ከተሞች እየተፈጸመ ያለውን ማንነትን መሰረት ያደረገ ጥቃት በማውገዝ ሰልፎች ተካሄዱ።

በሰለማዊ ሰልፎቹ “በተለያዩ አካባቢዎች በአማራዎች ላይ የሚፈጸም ግድያ ይቁም”፣ “አማራን ማሳደድ ይቁም”፣ “በአማራ ላይ እየተፈጸመ ያለው ጥቃትና መፈናቀል መንግሥትን ሊያሳስበው ይገባል የሚሉና ሌሎች መልዕክቶችም ተላልፈዋል፡፡

ችግሩን ለመፍታት መንግስት በትኩረተ ሊሰራ ይገባል ያሉት ሰልፈኞቹ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየተፈጠሩ ያሉ የጸጥታ መደፍረስ ችግሮች በአስቸኩዋይ  ሊቆሙ ይገባል ነው ያሉት።

በተለያዩ አካባቢዎች ማንነትን መሰረት አድርጎ የሚፈጸም ግድያ ይቁም፣ በብሄር ምክንያት ማሳደድ ይቁም፣ እየተፈጸሙ ያለው ግድያና መፈናቀሎች መቆም  ይገባቸዋል ብለዋል፡፡

በከድር መሀመድ እና ተጨማሪ መረጃ ከአሚኮ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!