Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድ ከ1ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ተሰበሰበ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 12፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከአሽከርካሪ ተሽከርካሪ ፈቃድና እድሳት ከ1 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የከተማዋ የአሽከርካሪ ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ገለጸ።

የትራፊክ መቆጣጠሪያ ደንብ በመተግበሩ የትራፊክ ስርዓትን የማክበር ተግባር መሻሻሉንም የከተማዋ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ አስታውቋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአሽከርካሪ ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አደም ኑሪ እንደገለጹት፤ በተያዘው በጀት ዓመት ባለፉት ዘጠኝ ወራት በተሽከርካሪ ቦሎ አገልግሎት፣ በመንጃ ፍቃድ እደሳና አዲስ በመስጠት ገቢ ተሰብስቧል።

በዚህም ለ43ሺህ ተገልጋዮች አዲስ መንጃ ፍቃድ መሰጠቱንና 263ሺህ የቦሎ አገልግሎት ለተሽከርካሪዎች መከናወኑን ተናግረዋል።

ባለፉት ዘጠኝ ወራት በተሰጡት አገልግሎቶች ለመሰብሰብ ከታቀደው 1 ነጥብ 19 ቢሊየን ብር ከእቅድ በላይ በማሳካት 1 ነጥብ 229 ቢሊየን ብር መሰብሰቡን አቶ አደም ጠቅሰዋል።

የገቢ መጠኑ ሊጨምር የቻለው የአገልግሎት ተደራሽነቱ በመስፋቱና በታሪፍ ላይ ቅናሽ በመደረጉ መሆኑን ገልጸዋል።

የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ ምክትል ዳይሬክተር ኢንጂነር ብርሃኑ ግርማ በበኩላቸው፤ ባለፉት ዘጠኝ ወራት የትራፊክ መቆጣጠሪያ ደንብ በመተግበሩ የትራፊክ ስርአትን የማክበር ተግባሩ መሻሻሉን መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ምክትል ዳይሬክተሩ እንዳሉት፤ በዘጠኝ ወራት ከትራፊክ ቅጣት ከ252 ሚሊዮን 882ሺህ ብር በላይ ና ከፓርኪንግ አገልግሎት ከ1 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ ተሰብስቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.