የሀገር ውስጥ ዜና

አቶ ተመስገን ጥሩነህ በሞጣ ከተማ የተቃጠሉና የተጎዱ የሃይማኖት ተቋማትን ጎበኙ

By Tibebu Kebede

January 17, 2020

አዲስ አበባ ፣ ጥር 8፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተመስገን ጥሩነህ በሞጣ ከተማ የተቃጠሉና የተጎዱ የሃይማኖት ተቋማትን ጎበኙ።

በጉብኝቱ ርዕሰ መስተዳድሩን ጨምሮ የአማራ ክልል የሰላምና ደህንነት ቢሮ ኃላፊ አቶ አገኘሁ ተሻገር፣ የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አበረ አዳሙ እና የሃይማኖት መሪዎች ተገኝተዋል።