A relative of a Covid-19 fatality wears personal protective equipment (PPE) while sitting on a bench outside a cremation hall at the Nigambodh Ghat crematorium in New Delhi India, on Monday, April 19, 2021. India has the world’s fastest-growing Covid-19 caseload behind only the U.S. in terms of total numbers. Photographer: T. Narayan/Bloomberg

ኮሮናቫይረስ

በህንድ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የሟቾች ቁጥር እየጨመረ ነው

By Abrham Fekede

April 21, 2021

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 13፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በህንድ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ከተከሰተ ጀምሮ በ24 ሰዓታት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ 2 ሺህ ሰዎች ለህልፈት ተዳረጉ፡፡

በተጨማሪም በኮሮና ቫይረስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥርም በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል ነው የተባለው፡፡

በ24 ሰዓታት ውስጥም 295 ሺህ 41 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል፡፡

ይህም ወረርሽኙ ከተከሰተ በኋላ ከፍተኛ ቁጥር ነው ተብሏል፡፡

በሀገሪቱ የመተንፈሻ ኦክስጅን እና የሆስፒታል አልጋዎች እጥረት ፈተና እንደሆነባቸው የጤና ባለሙያዎች አስታውቀዋል፡፡

የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ “ህንድ የኮሮና ቫይረስ አውሎንፋስ ገጥሟታል” ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

እስካሁን በህንድ በወረርሽኙ 15 ነጥብ 6 ሚሊየን ዜጎች ቫይረሱ ሲገኝባቸው፥ 182 ሺህ 553 ሰዎች ደግሞ ለህልፈት መዳረጋቸውን አልጀዚራ ዘግቧል፡፡

 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፦https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!