ስፓርት

መከላከያ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ መመለሱን አረጋገጠ

By Tibebu Kebede

April 21, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 13 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) መከላከያ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ መመለሱን አረጋግጧል፡፡

በከፍተኛ ሊግ በምድብ “ሀ” የሚወዳደረው መከላከያ በ2014 ዓ.ም የፕሪሚየር ሊግ ተሳታፊነቱን ያረጋገጠበትን ውጤት አስመዝግቧል፡፡

ዛሬ ከደብረብርሃን ጋር የተጫወተው መከላከያ በቴዎድሮስ ታፈሰ ጎል 1 ለ 0 አሸንፏል፡፡

ይህን ተከትሎም አንድ ጨዋታ እየቀረው ወደ ፕሪሚየር ሊጉ ዳግም ተመልሷል፡፡

መከላከያ በ2011 ዓ.ም ከፕሪሚየር ሊጉ መውረዱን የሶከር ኢትዮጵያ ዘገባ ያመላክታል፡፡

አዲስ አበባ ከተማ ከመከላከያ ቀደም ብሎ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ መመለሱ ይታወሳል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!