የአዲስ አበባ ከተማ አቀፍ የኪነ ጥበብ ሳምንት ነገ ይጀመራል
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 14፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)12ኛው የአዲስ አበባ ከተማ አቀፍ የኪነጥበብ ሳምንት ፌስቲቫል ነገ በግዮን ሆቴል ይጀመራል።
ኪነ ጥበብ ለሰላማችን እና ለአንድነታችን በሚል መሪ ቃል በሚካሄደው በዚህ ፌስቲቫል በርካታ ኪነጥበባዊ ስራዎች ለተደራሲያን ይቀርባሉ ተብሏል።
በዚህ ፌስቲቫል አንጋፋና ወጣት የትያትር ባለሙያዎች ፣የሙዚቃ ባለሙያዎች ፣ ሰዓሊያንና ቀራጺያንን ጨምሮ ሌሎች ባለድርሻ አካላት እንደሚሳተፉ ታውቋል፡፡
የአዲስ አበባ ባህል ኪነ ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ የኪነጥበብ ዘርፍ ምከትል የቢሮ ሃላፊ አቶ ሰርጸፍሬ ስብሃት በፌስቲቫሉ የግጥም፣ የፊልም፣የስዕል እና መሰል ከ20 በላይ የሚሆኑ የኪነጥበብ ዘርፎች ላይ ውድድሮች አንደሚካሄዱ ተናግረዋል፡፡
ፌስቲቫሉ ወጣት የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ከአንጋፋዎቹ ልምድ እንዲቀስሙ ከማድረጉም በላይ ለበርካታ ጀማሪ ባለሙያዎችም የመታያ መድረክ እንደሚሆን ይጠበቃል።
በተጨማሪም ፌስቲቫሉ በኮቪድ ምክንያት ተቀዛቅዞ የቆየውን የኪነ ጥበብ ዘርፍ ለማነቃቃት አጋዥ እንደሚሆን ተነግሯል።
ፌስቲቫሉ ለሶስት ቀናት የሚቆይ ሲሆን የኮሮና ቫይረስ ፕሮቶኮልን በጠበቀ መልኩ እንደሚካሄድ ተገልጿል፡፡
በትዝታ ደሳለኝ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፦https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!