Fana: At a Speed of Life!

የአሜሪካ ኤምባሲ በጸረ ሽብር ላይ ያተኮረ የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጠ 

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 15፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ በጸረ ሽብር ዙሪያ ያተኮረ የአቅም ግንባታ አውደ ጥናት አካሄደ፡፡

በአውደ ጥናቱ ላይ ዳኞች፣ ዐቃቤ ህጎች፣ ጠበቃዎች እና የማረሚያ ቤት አስተዳደር የስራ ሃላፊዎች ተሳትፈዋል፡፡

አውደ ጥናቱ በዋናነት ተሳታፊዎቹ በሽብርተኝነት ጉዳዮች ከልጆች ጋር ሲገናኙ የሚኖራቸውን ሚና ጨምሮ የተጠረጠረውን ልጅ በቁጥጥር ስር ከዋለበት ጊዜ ጀምሮ ጥቅሙን ማስከበር በሚችሉባቸው አግባቦች ላይ ትኩረቱን ያደረገ ነበር፡፡

ተሳታፊዎች በበኩላቸው አውደ ጥናቱ ሁሉን አቀፍ እና ያላቸውን ልምድ ለማዳበር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው መናገራቸውን ከአሜሪካ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፦https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.