ቢዝነስ

ለበዓሉ ወደ ጎንደር 19 ተጨማሪ በረራዎች ተዘጋጅተዋል

By Tibebu Kebede

January 17, 2020

አዲስ አበባ፣ ጥር 8፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጥምቀት በዓልን ምክንያት በማድረግ ከአዲስ አበባ ጎንደር ተጨማሪ 19 የበረራ መርሃ ግብር ማዘጋጀቱን አስታወቀ።

ለጥምቀት በዓልና ተያያዥ ጉዳዮች በቀጥታ ወደ ጎንደር የሚያመሩ 2 ሺህ 500 የሚደርሱ መንገደኞች መመዝገባቸውም ተመላክቷል።

አየር መንገዱ ከዚህ ቀደም ወደ ስፍራው በቀን ከአራት እስከ አምስት በረራዎች ይካሄዱ እንደነበር ጠቅሶ በዓሉን ምክንያት በማድረግ የበረራ ቁጥር መጨመሩን አስታውቋል።

ለጉዞ የተመዘገቡ መንገደኞች ትኬት እየቆረጡ መሆኑንና ያለውን አሃዝ በማየት አውሮፕላን መጨመር ካስፈለገ እንደሚጨመርም ነው የገለጸው።

የበረራ ትኬት ዋጋ ከዚህ ቀደም በነበረው መደበኛ ዋጋ እንደሆነ መግለጹንም ከአማራ መገናኛ ብዙሃን ድርጅት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።