የሀገር ውስጥ ዜና

ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ በኢትዮጵያ ከእስራኤል አምባሳደር ጋር ተወያዩ

By Tibebu Kebede

April 23, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 15 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ በኢትዮጵያ ከእስራኤል አምባሳደር አለልኝ አድማሱ ጋር ተወያዩ፡፡

በውይይታቸው ወቅትም በሁለቱ ሃገራት ግንኙነት ላይ የመከሩ ሲሆን፥ አምባሳደር አለልኝ ለዘመናት በታሪክ የሚገናኙትን ሃገራት ለማገልገል ቁርጠኛ መሆናቸውን ተናግረዋል።

አምባሳደሩ ከኢትዮጵያ ጋር በኢኮኖሚ ፣ ፖለቲካና የፀጥታ ጉዳዮች ላይ በትብብር ለመስራት መዘጋጀታቸውንም ነው የተናገሩት።

አምባሳደር አለልኝ አድማሱ በእስራኤል ፓርላማ አባል የነበሩ ሲሆን በቅርቡ በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር ሆነው መሾማቸው ከመከላከያ ሰራዊት ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!