የሀገር ውስጥ ዜና

ከ100 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነባው የእንስሳት መድኃኒት ፋብሪካ ተመረቀ

By Tibebu Kebede

April 24, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 16 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ብሔራዊ የእንስሳት ጤና ጥበቃ ኢንስቲቲዩት ከ100 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ በቢሾፍቱ ያስገነባው የእንስሳት መድኃኒት ፋብሪካ ተመረቀ።

የፋብሪካው ወደ ስራ መግባት ሃገሪቱ ለእንስሳት መድኀኒት የምታወጣውን ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ይቀንሳል ተብሏል ።

የብሔራዊ እንስሳት ጤና ጥበቃ ኢንስቲቲዩት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ማርታ ያሚን በምርቃት ስነስርዓቱ ላይ እንደተናገሩት ኢንስቲቲዩቱ የእንስሳት ክትባቶችን በማምረትና በማሰራጨት በተለይም ለግብርናው ዘርፍ ትልቅ እገዛ ሲያደርግ ቆይቷል።

ለተለያዩ ሃገራት የእንስሳት ክትባቶችን በመላክ የውጭ ምንዛሬ እያስገኘ መሆኑንም ገልጸው፤ ኢንስቲቲዩቱ ክትባቶችን በማምረት በተመጣጣኝ ዋጋ ከማቅረብ ባለፈ በክትባት ዙሪያ ምርምርና ጥናቶችን እየሰራ ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል። ቢሾፍቱ የሚገኘው ብሔራዊ የእንስሳት ጤና ጥበቃ ኢንስቲቲዩት በ1956 ዓ.ም የተመሰረተ መሆኑን መረጃዎች ይጠቁማሉ።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!