Fana: At a Speed of Life!

አብሮነታችን ለሀገራችን፣ ለሠላማችንና ለወንድማማችነት በሚል የማስ ስፖርት እንቅስቃሴ ተከናወነ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 17፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ክልል ስፖርት ኮሚሽን ከአዲስ አበባ ስፖርት ምክር ቤት ጋር በመተባበር አብሮነታችን ለሀገራችን፣ ለሰላማችንና ለወንድማማችነት በሚል በሀዋሳ ከተማ የማስ ስፖርት እንቅስቃሴ ተከናዉኗል፡፡
ስፖርትን ከኢኮኖሚዉ ፋይዳዉ ባሻገር ለሰላምና አንድነት እንዲሁም የመተባበር ሁኔታዎችን ምቹ የሚያደርግ በመሆኑ በየጊዜዉ ህዝቡን አሳታፊ ባደረገ መልኩ እንደሚካሄድ ተገልጿል፡፡
የክልሉ ባህል ቱሪዝም እና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃጎ አገኘው የሲዳማ ነዋሪዎች በያሉበት የስፖርት እንቅስቃሴዎችን በማጠናከር ለጤናዉ ጉልህ ሚና እንዲጫወት መነሳሳት ይገባል ብለዋል።
በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ አቶ ጥራቱ በየነ በበኩላቸዉ አገሪቷን አሁን እየገጠማት ያለዉን የሰላም እጦት ዘርፈ ብዙ ችግሮችን ለመቅረፍ አንድነትን የሚያጠናክሩ ስፖርት እንቅስቃሴዎችን ማጠናከር ይገባል ብለዋል፡፡
በስነ-ስረዓቱ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ስፖርት ኮሚሽን ለሲዳማ ክልል ስፖርት ኮምሽን የተለያዩ ኳሶችንና የኮምፒውተሮችን አበርክቷል፡፡
በታመነ አረጋ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.