የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የኢትዮጵያ በነጻነት የመልማት መብት ነው- ዶ/ር ኢንጂነር ስለሺ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 17፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የኢትዮጵያ በነጻነት የመልማት መብት በመሆኑ ሁሉም ኢትዮጵያዊ የጋራ አንድነት እና መግባባት ሊኖረው እና በጋራ በመቆም ከዳር ሊይደርሰው እንደሚገባ የውሃ፣መስኖ እና ኤሌክትሪክ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ክቡር ስለሺ በቀለ ገለፁ።
በካናዳ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ትብብር ለህዳሴ ግድብ በካናዳ ጋር በመተባበር በበይነ መረብ ውይይት አካሂደዋል።
በዚህ ወቅት ሚኒስትሩ ባደረጉት ንግግር ሁሉም ኢትዮጵያዊ የጋራ አንድነት እና መግባባት ሊኖረው እና በጋራ በመቆም ግደቡን ከዳር ሊይደርሰው እንደሚገባ እንዲሁም ዳያስፖራው የግድቡ አምባሳደር በመሆን የሀገሩን ፍትሀዊ ተጠቃሚነት እና መብት ለማሳወቅ እንዲረባረብ ጥሪ አቅርበዋል።
በሀገር ውስጥ በሚደረገው የቦንድ ግዢን በተመለከተ ዳያስፖራው አመቺ በሆነ እና የቢሮክራሲ ማነቆዎችን ባቃለለ መልኩ የተዘጋጁትን የቦንድ መግዣ መንገዶችን የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሃላፊ የሆኑት አቶ ለማ ዋቀዮ ገለጻ ማድረጋቸውን በካናዳ ከኢትዮጵያ ኤምባሲ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ በበኩላቸው፤ የዚህ ትውልድ አድዋ የሆነው ግድብ የኢትዮጵያውያንን ህይወት የሚቀይር በመሆኑ ሁሉም ተረባርቦ መጨረስ እንደሚገባና ሁሉም በእውቀት፣ ተፅዕኖ በማሳደር፣ በገንዝብ፣ በጉልበት እንዲሁም ባለው ነገር ሁሉ አስተዋጾ በማድረግ አሻራን ማኖር እንደሚገባ አሳስበዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡