ዓለምአቀፋዊ ዜና

በአፍሪካ በኮቪድ19 የተያዙ ሰዎች ቁጥር 4 ነጥብ 5 ሚሊየንን አለፈ

By Meseret Awoke

April 26, 2021

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 18፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በአፍሪካ በኮቪድ19 የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ4 ነጥብ 5 ሚሊየን አልፏል፡፡

በአህጉሪቱ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ የመጣ ሲሆን፤ ከ4 ሚሊየን 506 ሺህ በላይ ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል፡፡

እስካሁን በአህጉሪቱ በቫይረሱ ሳቢያ ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥርም ከ120 ሺህ በላይ ሆኗል፡፡

ደቡብ አፍሪካ፣ ሞሮኮ፣ ቱኒዚያ፣ ኢትዮጵያ እና ግብጽ ደግሞ ከፍተኛውን ቁጥር ይይዛሉ፡፡

በአንጻሩ ከ4 ሚሊየን በላይ ሰዎች ከቫይረሱ አገግመዋል፡፡

ምንጭ፡- ቢቢሲ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!