Fana: At a Speed of Life!

የ2ኛው ሀገራዊ የክህሎት፣ የቴክኖሎጂ፣ የተግባራዊ ጥናትና ምርምር ውድድር ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 18፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) ሁለተኛው ሀገራዊ የክህሎት፣ የቴክኖሎጂ፣ የተግባራዊ ጥናትና ምርምር ውድድር ተጠናቋል፡፡

ውድድሩ ከሚያዝያ 12 ቀን ጀምሮ በኢትዮጵያ ቴክኒካል ዩኒቨርሲቲ ሲካሄድ የቆየ ሲሆን፥ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አሸናፊነት መጠናቀቁን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ በሃገር አቀፍ ደረጃ ለሁለተኛ ጊዜ በተካሄደው ሁለተኛው ሀገራዊ የክህሎት፣ የቴክኖሎጂ፣ የተግባራዊ ጥናትና ምርምር ውድድር በበላይነት በማጠናቀቅ የዋንጫ ተሸላሚ ሆኗል፡፡

ኤጀንሲው ከኮሌጅ ጀምሮ በክላስተር ደረጃ እንዲሁም በከተማ ደረጃ በተካሄደው የክህሎት ውድድር የተሻለ ውጤት ያስመዘገቡ ተወዳዳሪዎች በሃገር አቀፍ ደረጃ በአሰልጣኝ፣ በሰልጣኝና በአንቀሳቃሽ ምድብ ተከፍሎ ሲካሄድ ቆይቷል፡፡

በዛሬው ዕለት በተካሄደው የዕውቅና መርሃ ግብር በኤጀንሲ ስር በሚገኙ የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች የተለያዩ ችግር ፈቺ ቴክኖሎጂዎችን የፈጠሩ አሰልጣኞችና ሰልጣኞች የሰርተፍኬትና በተለያዩ የሙያ መስኮች ተመዝነዋል፡፡

በዚህም ከ1ኛ እስከ 3ኛ ደረጃ ለያዙ ተወዳዳሪዎች 30 ሜዳሊያዎች የተበረከተላቸው ሲሆን፤ ከአንድ እስከ ሶስተኛ ለወጡ ተሸላሚዎች ከ25 ሺህ ብር ጀምሮ የ20 ሺህ ብር ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.