የሀገር ውስጥ ዜና

በጅግጅጋ ከተማ በ60 ሚሊየን ብር ለሚገነባው ቤተ መጽሐፍት የመሰረት ድንጋይ ተጣለ

By Tibebu Kebede

April 26, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 18 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በጅግጅጋ ከተማ በ60 ሚሊየን ብር ለሚገነባው የህዝብ ቤተ መጽሐፍት የመሰረት ድንጋይ ተጣለ፡፡

የመሰረት ድንጋዩ የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ዑመርን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት ነው የተጣለው፡፡

ለቤተ መጽሐፍቱ የሚወጣው ወጪ ሙሉ በሙሉ በክልሉ መንግስትና ከህዝብ በሚሰበሰብ ገንዘብ እንደሚሸፈን ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ በፌስ ቡክ ገጻቸው አስታውቀዋል፡፡

ቤተ መጽሐፍቱ በምስራቅ አፍሪካም በአይነቱ የመጀመሪያ እንደሆነም ገልጸዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!