ለኤካ ኮተቤ ጠቅላላ ሆስፒታል 20 ሚሊየን ብር ግምት ያላቸው የሕከምና ቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገለት
አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 19 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የቻይና ንግድ ምክር ቤት ለኤካ ኮተቤ ጠቅላላ ሆስፒታል 20 ሚሊየን ብር ግምት ያላቸው የተለያዩ የሕከምና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።
ድጋፉ አንድ አምቡላንስ፣ 16 ሰው ሰራሽ የመተንፈሻ መሳሪያ፣ አራት የፅኑ ሕሙማን አልጋዎችና ሌሎች የሕክምና ቁሳቁሶችን ያካተተ ነው።
የተበረከተውን ድጋፍ የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ዓለምፀሃይ ጳውሎስ እና የሆስፒታሉ ዋና ስራ አስኪያጅ ዶክተር ያሬድ አግደው ተረክበዋል።
በርክክቡ ላይ በኢትዮጵያ የቻይና ኤምባሲ ካውንስለር ሊዩ ዩ ተገኝተዋል።
የሕክምና ቁሳቁሱ የጽኑ ታማሚዎችን ለማከምና ወረርሽኙን ለመከላከል እንደሚያግዝ መገለጹን ኢዜአ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!