የሀገር ውስጥ ዜና

ወይዘሮ መዓዛ አሸናፊ በኢትዮጵያ ከአሜሪካ አምባሳደር ጋር ተወያዩ

By Tibebu Kebede

April 28, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 20 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት መዓዛ አሸናፊ በኢትዮጵያ ከአሜሪካ አምባሳደር ጊታ ፓሲ ጋር ተወያዩ፡፡

በውይይታቸው ወቅት አሜሪካ ለኢትዮጵያ የፍትህ ዘርፍ ማሻሻያ በምታደርገው ድጋፍና እርዳታ ዙሪያ መክረዋል፡፡

አምባሳደር ጊታ ፓሲ የፍትህ ስርአቱን ነጻና ገለልተኛ ለማድረግ በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሚደረጉ ጥረቶችን አድንቀዋል፡፡

አያይዘውም በኢትዮጵያ እና አሜሪካ መካከል ያለው አጋርነት እንደሚቀጥል መግለጻቸውን የአሜሪካ ኤምባሲ መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!