ኮሮናቫይረስ

ከኮሮና ቫይረስ ጋር ተያይዞ 940 ፅኑ ህሙማን ሲገኙ ፤ የ34 ሰዎች ህይወት አልፏል

By Tibebu Kebede

April 28, 2021

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 20፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት 7 ሺህ 99 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 1 ሺህ 244

ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ አሁን ላይ በፅኑ ህሙማን ክፍል 940 ሰዎች የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል ተብሏል።

ባለፉት 24 ሰዓታት 877 ሰዎች ከቫይረሱ ያገገሙ ሲሆን 34 ሰዎች ደግሞ ህይወታቸው አልፏል።