የሀገር ውስጥ ዜና

መከላከያ ሚኒስቴር በአጣዬና አካባቢው ለተፈናቀሉ ወገኖች የ2 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

By Meseret Awoke

April 30, 2021

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 22፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)የኢፌድሪ መከላከያ ሚኒስቴር በአጣዬ እና አካባቢው በተፈጠረ ግጭት ለተፈናቀሉ ወገኖች የሚውል የ2 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ።

ድጋፉን የመከላከያ ሚኒስትሩ ዶክተር ቀንኣ ያደታ ለአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳደር ዶክተር ፋንታ ማንደፍሮ አስረክበዋል።

በአጣዬና አካባቢው በተከሰተው የጸጥታ ችግር ምክንያት የደረሰውን የንብረት ውድመትና ኪሳራ መሰረት አድርጎ ድጋፍ ማድረጉን ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

ሰራዊቱ እየከፈለ ከሚገኘው የህይወት መስዕዋትነት ባሻገር መሰል ድጋፍ በማድረግ ለተጎጂዎች ለመድረስ ጥረት እያደረገ መሆኑም ተገልጿል።

ከዚህ ውስጥ 1 ሚሊዬኑ ለአጣዬ 1 ሚሊዬኑ ደግሞ ለከሚሴ እንደሆነ ተገልጿል።

መከላከያ ምንጊዜም ከህዝቡ ጎን ቆሞ እየተጋ ነው ያሉት ሚኒስትሩ፤ ከህዝብ አብራክ የወጣ እንደመሆኑ ተጎጂ ለሆኑ ወገኖች ለመድረስ ያደረገው ድጋፍ ነው ብለዋል።

ድጋፉ በሁሉም ረገድ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባም ገልፀዋል።

ምክትል ርዕሰ መስተዳደሩ በበኩላቸው፤ የመከላከያ ሚኒስቴር ለወገን ደራሽነቱን በአርአያነት በማሳየት ላሳየው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።

በሀብታሙ ተ/ስላሴ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!