የሀገር ውስጥ ዜና

የከተማው አስተዳደር ያዘጋጀው የጸሎተ ሀሙስ እና የረመዳን የኢፍጣር መርሐግብር ትናንት ምሽት ተካሂዷል

By Meseret Awoke

April 30, 2021

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 22፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ያዘጋጀው የጸሎተ ሀሙስ እና የረመዳን የኢፍጣር መርሐግብር በትናንትና ምሽት መካሄዱ ተገለጸ። በመርሐግብሩ ላይ የየሀይማኖት ተቋማቱ መሪዎች ስለሰላም፣ስለአብሮነት ፣አንድነት እና መቻቻል መልዕክት አስተላልፈዋል ።

የጸሎተ ሀሙስ እና የረመዳን የኢፍጣር መርሐግብር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ፣የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የቅድስት ስላሴ መንፈሳዊ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት አቡነ ፍሊጶስ ፣የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጂ ኡመር እድሪስ ፣የወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ህብረት ፕሬዚዳንት ፓስተር ጻዲቁ አብዶ እና የሁሉም ሀይማኖት ተቋማት መሪዎች እና የእምነቱ ተከታዮች በተገኙበት በስካይላይት ሆቴል ተካሂዷል።

ኢትዮጵያ የተለያዩ ሀይማኖቶች ፣ብሄሮች እና ቋንቋዎች ሳያለያዩ እንደሰርገኛ ጤፍ አንድ የሆኑባት ድንቅ ሀገር ነች ብለዋል ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ።

እኛ ኢትዮጵያዊያን አንድ ሀገር፣ አንድ ስነልቦና ያለን አብሮነታችንና አንድነታችን ለአለም ምሳሌ የሆንን ህዝቦች ነን ያሉት ምክትል ከንቲባዋ፤ ይህ መቻቻል እና መከባበር ለአንድነታችን እና ለታላቅነታችን መሰረት በመሆኑ ተጠናክሮ እና ዳብሮ መቀጠል ይኖርበታል ማለታቸውን ከከተማው አስተዳደሩ ፕሬስ ሴክሬተሪያት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!