የሀገር ውስጥ ዜና

ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸዉ የፋሲካ በአልን ምክንያት በማድረግ ለአይነስዉራን ማዕድ አጋሩ

By Meseret Awoke

April 30, 2021

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 22፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸዉ የፋሲካ በአልን ምክንያት በማድረግ ለ100 አይነስዉራን ማዕድ አጋርተዋል፡፡

የቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት ከዚህ ቀደም በኮሮና ወረርሽኝ ወቅት ከጠቅላይ ሚኒስትሩ የመጣዉን ማእድ የማጋራት ጥሪ በመቀበል ለአካል ጉዳተኞች ማእድ ማጋራቱ ይታወሳል፡፡

ጽህፈት ቤቱ ለአካል ጉዳተኞች ትኩረት በመስጠት የተለያዩ ድጋፎችን ሲያደርግ የቆየ ሲሆን፤ ወደፊትም በተለያዩ እንቅስቃሴዎች ለአካል ጉዳተኞች የሚያደርገዉን ድጋፍ እንደሚቀጥልም ነው ከጽህፈት ቤቱ ያገኘነው መረጃ የሚያመላክተው፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!