የሀገር ውስጥ ዜና

በአዲስ አበባ የመጀመሪያው አቅም የሌላቸው ዜጎች የምገባ ማዕከል ተመረቀ

By Amare Asrat

May 02, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 24፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) – በአራዳ ክፍለ ከተማ የመጀመሪያው የምገባ ማዕከል ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በተገኙበት ተመርቆ ሥራ ጀመረ፡

“የተስፋ ብርሃን ምገባ ማዕከል” በሚል ስያሜ ወደ ስራ የገባው ማዕከል ከ800 በላይ የሚሆኑ አቅም የሌላቸው ነዋሪዎችን በቀን አንድ ጊዜ መመገብ የሚያስችል ነው ተብሏል።

በከተማዋ ወደ መሰል ስራ ለመግባት በሂደት ላይ ካሉ 5 ማዕከላት መካከል አንዱ የሆነው ይህ ማዕከል የመመገቢያና እና የማብሰያ ቦታዎችን አካቶ የተገነባ ነው።

አንድ መቶ ሺህ የሚደርሱ ዜጎች በቀን አንድ ጊዜ እንኳ መመገብ የማይችሉ መሆናቸው በጥናት በመረጋገጡ በሂደት ሁሉንም ወደ ምገባው ለማምጥትና በቀን አንድ ጊዜ የነበረውን ወደ ሁለት ለማሳደግ እንደታቀደ ተገልጿል።

በማዕከሉ የሚካሄደውን የምገባ መርሃ ግብር ፈቃደኛ ባለሃብቶችና ሆቴሎች እንደሚደግፉት ተነግሯል።

በሀብታሙ ተ/ስላሴ