የሀገር ውስጥ ዜና

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በአፍሪካ ምርጡ 10ኛ ዩኒቨርሲቲ ተባለ

By Tibebu Kebede

May 03, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 25 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በአፍሪካ ምርጡ 10ኛ ዩኒቨርሲቲ ተባለ።

ዩኤስ ኒውስ ግሎባል ዘንድሮ ባወጣው ደረጃ መሰረት ዩኒቨርሲቲው ከአፍሪካ ዩኒቨርሲቲዎች 10ኛ ደረጃ ሲይዝ በምስራቅ አፍሪካ ደግሞ ቀዳሚ ሆኗል።

በዓለም ላይ ካሉ ዩኒቨርሲቲዎች አንጻር ደግሞ 553ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

ባለፈው አመት ኒውስ ግሎባል ባወጣው ደረጃ ከምስራቅ አፍሪካ ዩኒቨርሲቲዎች 2ኛ እንዲሁም ከዓለም 616ኛ ደረጃ ላይ የነበረው ዩኒቨርሲቲው ዘንድሮ ደረጃውን አሻሽሏል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!