Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ፋርማጆ የኢትዮጵያን እና ሶማሊያን ግንኙነት ለማጠናከር እንደሚሰሩ አስታወቁ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 25፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሶማሊያ የኢትዮጵያ አምባሳደር አቡዱልፈታህ አብዱላሂ የሹመት ደብዳቤያቸውን ለሶማሊያው ፕሬዚዳንት መሀመድ ፋርማጆ አቅርበዋል።

በዚህ ወቅትም ፕሬዚዳንት ፋርማጆ የሁለቱን ሃገራት ግንኙነት ለማጠናከር እንደሚሰሩ አስታውቀዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም ቀጠናዊ ትብብርን እና ስትራቴጂካዊ አጋርነትን ለማጠናከር እንደሚሰሩ መናገራቸውን የሶማሊያ መንግስት ቃል አቀባይና የጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚዲያ ከፍተኛ አማካሪ ሙሃመድ ኢብራሂም ሞዓሊሙ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡

አምባሳደር አቡዱልፈታህ አብዱላሂ የሹመት ደብዳቤያቸውን ባቀረቡበት ወቅት ከፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የተላከን መልዕክት ለፕሬዚዳንት መሀመድ ፋርማጆ አቅርበዋል።

አምባሳደር አቡዱልፈታህ አብዱላሂ የኢትዮጵያን እና ሶማሊያን ግንኙነት ማጠናከር አስፈላጊ መሆኑን እና የሀገራቱን ሉዓላዊነት ማስጠበቅ ወሳኝ መሆኑን አስረድተዋል።

ፕሬዚዳንት መሀመድ ፋርማጆ የሶማሊያ መንግስት አስተዳደርን ለማጠናከር ፣የኢኮኖሚ እድገት ለማምጣት ፣ ሙስናን ለመከላከል እና ሽብርተኝነት ለመዋጋት እያከናወነች ስለሚገኘው ስራ ለአምባሳደሩ ገልጸውላቸዋል፡፡

ሶማሊያ  በትብብር ፣ በመልካም ጉርብትና እና በመተባበር መንፈስ ግንኙነቷ እንዲጠናከር ያላትን ፍላጎትም ገልፀዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.