የሀገር ውስጥ ዜና

አምባሳደር ሳሚያ ዘካሪያ በኳታር ከዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት ኃላፊ ጋር ተወያዩ

By Tibebu Kebede

May 03, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 25 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኳታር የኢፌዴሪ አምባሳደር ሳሚያ ዘካሪያ በኳታር የዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት ኃላፊ ኢማን ኤሪይቃት ጋር ተወያዩ፡፡

በውይይታቸው ወቅትም በኳታር በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ሰራተኞችን ጉዳይ በተመለከተ መምከራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

በኳታር የሚገኘው ኤምባሲም የዜጎቹ መብት እንዲከበር እያደረገ ያለውን ጥረት በማብራራት፥ ድርጅታቸው በኳታር ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያውን ሰራተኞች ለሚደርስባቸው ችግሮች ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም በኢትዮጵያ እና በቀጠናው ያለውን ወቅታዊ ጉዳዮች በተመለከተም ላሃላፊዋ ገለጻ አድርገውላቸዋል፡፡

የዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት ኃላፊ ኢማን ኤሪይቃት በበኩላቸው፥ ከኤምባሲው ጋር ተቀራርቦ ለመሥራት እና ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!