የሀገር ውስጥ ዜና

የዓለም የፕረስ ነፃነት ቀን እየተከበረ ነው

By Tibebu Kebede

May 04, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 26 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም የፕረስ ነፃነት ቀን “መረጃ ለህዝብ ጥቅም በሚል መሪ ሃሳብ” እየተከበረ ነው።

ዛሬ እየተከበረ ባለው የዓለም የፕረስ ነፃነት ቀን የሚዲያ አካላት እና ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ነው ።

ጋዜጠኞች ከስጋት ነፃ ሆነው የሚሰሩበት እና ዜጎች ትክክለኛ መረጃ ማግኘት የሚችሉበትን እድል መፍጠር እንደሚያስፈልግ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ምክር ቤት ሰብሳቢ ትዕግስት ይልማ ተናግረዋል።

መገናኘኛብዙሃን እና ባለሙያዎች በማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ የሚስተዋሉ የጥላቻ ንግግሮችን በመቆጣጠር ሃላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባም መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

በይስማው አደራው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!